ሪያል ማድሪድ ከ ባየርን ሙኒክ ፤ ስፖርቲንግ ከ አርሰናል ፦ የቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች

You are currently viewing ሪያል ማድሪድ ከ ባየርን ሙኒክ ፤ ስፖርቲንግ ከ አርሰናል ፦ የቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች

AMN-መጋቢት 29/2018 ዓ.ም

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ። ሪያል ማድሪድ ከ ባየርን ሙኒክ በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ የሚያደርጉት ጨዋታ የዕለቱ ተጠባቂ ፍልሚያ ነው።

በጋራ 21 የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ያሸነፉት ሁለቱ የአህጉሪቱ ሃያላን ክለቦች ለ29ኛ ጊዜ ይገናኛሉ። በውድድሩ ታሪክ በዚህ መጠን እርስ በእርስ የተገናኙ ክለቦች የሉም።

የስፔኑ ክለብ 13ቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ሲወስድ ፣ ባየርን ሙኒክ 11 ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።

ሪያል ማድሪድ በውድድር ዓመቱ ብቸኛ የዋንጫ ተስፋው ቻምፒየንስ ሊግ ይመስላል። ማሪንጌዎቹ በሳምንቱ መጨረሻ በማዮርካ ተሸንፈው ከመሪው ባርሰሎና በሰባት ነጥብ ርቀዋል።

ከዣቪ አሎንሶ ተረክቦ በጊዜያዊነት ቡድኑን እየመራ የሚገኘው አልቫሮ አርቤሎዋ ቦታውን ለማደላደል በቻምፒየንስ ሊጉ የተሻለ ውጤት ማምጣት ይጠበቅበታል።

የ15 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ማድሪድ ዛሬ የሚያከናውነው 41ኛ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ነው። በቪንሰንት ኮምፓኒ እየተመራ ድንቅ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው ሙኒክ በአውሮፓ ከሚፈሩ ክለቦች እንደ አንዱ ይቆጠራል።

በተለይ የማጥቃት ሃይሉ እጅግ አስፈሪ ሲሆን ፣ በቡንደስሊጋው ብቻ በ28 ጨዋታዎች 100 ግብ አስመዝግቧል። ይህ ቁጥር አስተማማኝ የተከላካይ ክፍል ለሌለው ሪያል ማድሪድ ትልቅ ስጋት ይሆናል። የስድስት ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ሙኒክ 36ኛ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ያከናውናል።

የጀርመኑ ክለብ በዘንድሮው ውድድር በሊግ ምዕራፍ አርሰናልን ተከትሎ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ፣ በጥሎ ማለፍ ዙር አታላንታን በድምር ውጤት 10ለ2 በመርታት ነው ለዛሬው ጨዋታ የበቃው።

በዛሬ ጨዋታ በማድሪድ በኩል ጁድ ቤሊንግሃም እና ኪሊያን ምባፔ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ይካታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሙኒክ በኩል ከጉዳት ያገገመው ሀሪ ኬን ከስብስቡ ጋር ወደ ማድሪድ ተጉዟል።

እንግሊዛዊው ዋና ዳኛ ማይክል ኦሊቨር የሚመሩት ተጠባቂው ጨዋታ ምሽት 3:45 ይጀምራል። በተመሳሳይ ምሽት 3:45 አርሰናል በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም ስፖርቲንግ ሊዝበንን ይገጥማል።

በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት ተከታታይ ጨዋታ በማንችስተር ሲቲ እና ሳውዛምፕተን ተሸንፎ ከሁለት ውድድር ውጪ የሆነው አርሰናል ወደ ድል ለመመለስ ይፋለማል።

መድፈኞቹ የፖርቹጋሉን ክለብ አምስት ጊዜ ገጥመው በአንዱም አልተሸነፉም። ሁለቱን አሸንፈው ሦስቱን በአቻ ደምድመዋል። ለመጨረሻ ጊዜ በተገናኙበት የባለፈው ዓመት ጨዋታ አርሰናል ዛሬ በሚጫወትበት ሜዳ 5ለ1 ማሸነፉ ይታወሳል። በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ ለመሆን የሚጥረው ስፖርቲንግ በተለይ በሜዳው ጠንካራ ክለብ መሆኑን አሳይቷል።

አርሰናል ሰሞነኛ ብቃቱ ጥሩ ባይሆንም በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያለው ጥንካሬ ግን አስደማሚ ነው። የሚካኤል አርቴታው ቡድን በሊግ ምዕራፍ ስምንቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ ታሪክ ሰርቶ ነበር ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለው። በጥሎ ማለፉም ባየርን ሊቨርኩሰንን በድምር ውጤት 3ለ1 አሸንፏል።

በዛሬው ጨዋታ በልዩነት የሚጠበቀው የቪክቶር ዮኬሬሽ ወደ ቀድሞ ቤቱ መመለስ ነው። ስዊድናዊው አጥቂ በስፖርቲንግ ሊዝበን ቆይታው 102 ጨዋታዎችን አከናውኖ 97 ግቦችን አስቆጥሯል።

በስፖርቲንግ ደጋፊዎች ተወዳጅ የነበረው አጥቂ ክለቡን ለመልቀቅ የመረጠው መንገድ ግን አይንህን ለአፍር እንዲሉ አድርጓቸዋል።

በዚህ ምክንያት ዮኬሬሽ ጠንከር ያለ ተቃውሞ ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review