በበዓላት ገበያ በተደረገ የቁጥጥር ዘመቻ የጤና ስጋት የሆኑ ምርቶችን ከገበያ ማስወገድ ተችሏል- ባለስልጣኑ

You are currently viewing በበዓላት ገበያ በተደረገ የቁጥጥር ዘመቻ የጤና ስጋት የሆኑ ምርቶችን ከገበያ ማስወገድ ተችሏል- ባለስልጣኑ

AMN-መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የረመዳንና የፋሲካ በዓላትን መነሻ በማድረግ ባከናወነው ድንገተኛ የቁጥጥር ዘመቻ፣ ለጤና አስጊ ሆነው የተገኙ የንግድ ምርቶችን ከገበያ ማስወጣቱን ገለጸ።

የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያከናወነውን ሰፊ የቁጥጥር ሥራና የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ እንጋ እርቀታ፣ በቁጥጥር ዘመቻው በሁሉም የከተማዋ የባዛር ቦታዎች፣ የባልትና ውጤቶች ማምረቻዎች፣ ወፍጮ ቤቶች እና የምግብ ማከፋፈያ ተቋማት ላይ ጥብቅ ፍተሻ መካሄዱን ተናግረዋል።

በተደረገው ፍተሻም ለጤና አስጊ ሆነው የተገኙ የጠረጴዛ ጨው፣ የታሸጉ ውሃዎች፣ የቴምር እና የበርበሬ ምርቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ከገበያ እንዲወገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ሸማቾች ማንኛውንም ምርት ሲገዙ የመጠቀሚያ ጊዜንና የጥራት ምልክቶችን የመፈተሽ ልምድ እንዲያዳብሩ ያሳሰቡት ምክትል ሥራ አስኪያጁ፣ ህገ-ወጥ ተግባራትን ሲመለከቱ በ8864 ነፃ የጥሪ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ አቅርበዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review