7ኛው ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ኮንፍረንስ ሚያዚያ 7 እና 8 በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ ይካሄዳል

You are currently viewing 7ኛው ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ኮንፍረንስ ሚያዚያ 7 እና 8 በቤንሻንጉል ጉሙዝ አሶሳ ከተማ ይካሄዳል

AMN መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

‎የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 7ኛው ሀገር አቀፍ ጉባኤን በማስመልከት መግለጫ ሰቷል።

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ 7ኛው ሀገር አቀፍ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቤንሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ከተማ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል ።

ሃይማኖቶች ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት እንዲጎለብት ያላቸው ሚና የሚንፀባረቅበት ኮንፍረስ መሆኑን መግለጫው አትቷል።

በሀገር ያለውን ሰላም ለማፅናት የሀይማኖት ተቋማት ግንባር ቀደም የሰላም ሰባኪ እንዲሆኑ ለማስቻልና ለማገዝ ያለመ ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ ነው ብለዋል።

በጉባኤው ባለፉት በተካሄዱት ጉባኤ የተገኙ ውጤቶችን በማላቅ በሀገራችን ዘላቂ ሰላምን ለማፅናት ያለመ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ተቋማት በልማትና በሰላም ግንባታ የጎለ ድርሻ የሚወጡበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል ።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review