AMN- መጋቢት 30/2018ዓ.ም
ወጣቶች የምርጫ ካርድ ከመውሰድ በተጨማሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች ወጣቶችን አስመልክቶ የሚያቀርቧቸውን ማኒፌስቶዎች በትኩረት መመርመር እንደሚገባቸዉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ዘርፍ ሚንስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ ተናገሩ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ በሚል መሪ ሀሳብ የወጣቶች ግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር አካሂዷል።
ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሙና አህመድ ያለፉት አመታት የነበረው የወጣቶች ተሳትፎ በቂ የሚባል እንዳልነበር አስታውሰው ቀደም ብሎ በተካሄደው 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ወጣቶች በመመረጥ አንዲሁም ምርጫን በማስፈፀም ሂደት ወስጥ 150 ሺህ ወጣቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል ብለዋል ።
ይህም ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ መሠረት የጣለ ስለመሆኑ አንስተዋል።
የወጣቶች የምርጫ ካርድ ከመውሰድ በተጨማሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚያቀርቧቸውን ማኒፌስቶዎች ላይ ለወጣቶች የተሰጠውን ትኩረት መመርመር ይገባቸዋልም ብለዋል ።
በወንድምአገኝ አበበ