AMN መጋቢት 30/2018
ጥራቱ ያልተረጋገጠ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ላይ ህጋዊ ዓርማ አስመስለው ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ፓስተር ዓለም ፀሀይ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሀሰተኛ የቤት ክዳን ቆርቆሮ ላይ ህጋዊ ለማስመስል ሀሰተኛ ማህተም በማዘጋጀት ሲጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች ላይ ከህብረተሰቡ በደረሰ መረጃ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻና ብርበራም በአንድ ግለሰብ መጋዘን ውስጥ 4ሺህ391 የቤት ክዳን ቆርቆሮ ላይ ህገ ወጥ አርማ በማዘጋጀት ሲያትሙ የነበሩ ሠባት ተጠርጣሪዎችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸውም ችሏል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢው ምርመራ ማስፋት ስራን በመስራት ክስ እንደሚመሰርት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።