ተቋማት በቅንጅት መስራታቸው በአጭር ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ከግብ እንዲደርሱ አስችሏል

You are currently viewing ተቋማት በቅንጅት መስራታቸው በአጭር ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ከግብ እንዲደርሱ አስችሏል

AMN- ሚያዝያ O1/2018 ዓ.ም

ተቋማት በቅንጅት መስራታቸው እቅዶች በጥራት፣ በአጭር ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ከግብ እንዲደርሱ አስችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የቅንጅታዊ ስራዎች የማህበራዊ ልማት ክላስተር የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የክላስተሩ ሰብሳቢ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ክላስተሩ ያቀፋቸው 11 ተቋማት በጋራ መስራታቸው እቅዶች በጥራት፣ በአጭር ጊዜ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ከግብ እንዲደርሱ ማስቻሉን ገልፀዋል። ነዋሪዎችም ደረጃቸውን የጠበቁ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ሚናው የላቀ መሆኑ ተነስቷል።

ትምህርት ቢሮ፣ ጤና ቢሮ፣ ምገባ ኤጀንሲን ጨምሮ 11 ቢሮዎች እና ተቋማት የቅንጅታዊ ስራዎች የማህበራዊ ልማት ክላስተር አባል ናቸው። ክላስተሩ እያካሄደ የሚገኘው መድረክ

ቀደም ሲል ካካሄደው ከ6 ወራቱ እቅድ አፈፃፀም በኋላ የተከናወኑ ተግባራት ምን ይመስላሉ የሚለው የሚፈተሽበት፣ ቅንጅታዊ አሰራር ያመጣቸው ውጤቶች የሚገመገሙበት ብሎም የቀሪ ሦስት ወራት አቅጣጫ የሚቀመጥበት ነው።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review