የጸሎተ ሐሙስ የእግር ማጠብ ሥርዓት ምስጢርና ትርጉም

You are currently viewing የጸሎተ ሐሙስ የእግር ማጠብ ሥርዓት ምስጢርና ትርጉም

AMN – ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ በጸሎተ ሐሙስ የሚከናወነው የእግር ማጠብ ሥርዓት፣ ከሃይማኖታዊ ክንውንነቱ ባለፈ ለሰው ልጅ ሁሉ ትልቅ የትሕትና እና የፍቅር መማሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።

የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን የሆኑት መጋቢ ምስጥረ አዕመረ ፀሐይ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሥርዓቱን መነሻና ፋይዳ በዝርዝር አብራርተዋል።

እንደ መጋቢ ምስጥረ ማብራሪያ፤ ሥርዓቱ ኢየሱስ ክርስቶስ በትሕትና ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር ካጠበበት ታሪካዊ ድርጊት የሚመነጭ ነው።

በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 13 ላይ በተጠቀሰው መሠረት፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ወገቡን ታጥቆ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቧል።

ይህ ተግባር ፈጣሪና ጌታ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ ማገልገልን የሚያሳይ ሲሆን፣ አማኞችም እርስ በእርሳቸው እንዲከባበሩና በትሕትና እንዲያገለግሉ ለማስተማር የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የቤተክርስቲያን አባቶችና ፓትርያርኩ ካህናትንና ምዕመናንን እግር የሚያጥቡት ይህንን የክርስቶስን አርአያነት በመከተል ነው።

ይህም ለዛሬው ትውልድ በመከባበር፣ በመተሳሰበና በፍቅር አብሮ የመኖርን ጥልቅ ትርጉም የሚያስተምር ታላቅ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርት መሆኑን መጋቢ ምስጥረ አዕመረ ፀሐይ አስገንዝበዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review