AMN ሚያዝያ 01/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ መሰረት ሐሙስ ኢየሱስ ክርስቶስ የደቀመዛሙርቱን ዕግር ያጠበበትና እናንተም ለታናኖሾቻችሁ ይህን አድርጉ ሲል ትህትናን ያስተማረበት ዕለት ነው።
በዚህች ዕለት ምሽትም እየሱስ ክርስቶስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የተመገበበትና ሚስጥረ ቁርባን የተገለጠበት መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ታስተምራለች።
በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሊቃነ ጳጳሳት የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በተገኙበት በዓሉ በመከበር ላይ ነው።

በቤተክርስቲያኗ አድባራትና ገዳማት የዛሬው በዓል በማለዳ ኪዳን፣ በስግደት፣ በህፅበት እግር፣ በቅዳሴና ሌሎችም መንፈሳዊ መርሀግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በቤተልሔም አየነው