የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የእንስሳት እርድ አገልግሎቱን በአምስት እጥፍ ማሳደጉን ገለጸ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የእንስሳት እርድ አገልግሎቱን በአምስት እጥፍ ማሳደጉን ገለጸ

AMN – ሚያዝያ 02/ 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት መዲናዋን የሚመጥን ዘመናዊ የእንስሳት እርድ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ባለዉ ስራዎች የእርድ አገልግሎቱን በአምስት እጥፍ ማሳደጉን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉነህ ዳሳለኝ ገለጹ፡፡

አቶ ሙሉነህ ዳሳለኝ በተለይ ለኤኤምኤን እንደተናገሩት ድርጅቱ የእንስሳት እርድ አገልግሎትን ለማዘመን በሰራቸዉ በርካታ ስራዎች ለዓመታት ሲጠቀምባቸው የነበሩ አድካሚ የአሰራር ዘዴዎችን ወደ ዘመናዊ ክፍሎችና ቴክኖሎጂዎች ቀይሯል፡፡

በአጭር ጊዜ ዉስጥ በተከናወኑ ስራዎች የእርድ አገልግሎቱን በቀን ከ200 በሬዎች ወደ 1ሺህ በማሳደግ የእርድ አገልግሎቱን ፈጣን፤ ቀላል እና ዉጤታማ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተንኳይ ጆክ በበኩላቸው፣ ከተማዋን ዲጂታል ለማድረግና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየተደረገ ባለዉ ጥረት የቄራዎች ድርጅት የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረጉ በአርአያነት የሚጠቀስ ነዉ፡፡

አቶ ተንኳይ ጆክ አክለውም ድርጅቱ አገልግሎቱን ማዘመኑ ለከተማው ነዋሪዎች ጥራቱን የጠበቀ የሥጋ ምርት በተገቢው ፍጥነት ለማቅረብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አብራርተው፣ በድርጅቱ የተጀመረው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሌሎች የልማት ድርጅቶችም በዚሁ መንገድ አሰራራቸውን እና አገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያዘሙኑ የተወጠነው እቅድ አካል እንደሆነም ገልጸዋል።

በድርጅቱ ውስጥ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ አንዳንድ ሰራተኞችም ቀደም ሲል የነበረው አሰራር እጅግ አድካሚና ለተለያዩ አደጋዎች የሚዳርግ እንደነበር ገልጸዉ አሁን ላይ ተግባራዊ የተደረገዉ የእርድ አገልግሎት ምቹ የስራ አካባቢን የፈጠረና የሥራ ጫናን የቀነሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review