AMN- ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም
በክርስትና እምነት አስተምህሮት መሰረት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሰዉ ልጆችን ከሃጢአታቸዉ ያዳናቸዉ ዕለት በጾም፤ በጸሎት፤ በስግደት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየታሰበ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችም በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያናት በመገኘት የስቅለት በዓልን በተለያዩ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብሮች እያሰቡት ይገኛሉ፡፡
ዕለቱ በሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድም በተለያዩ ሃይማኖታዊ መርሃ ግብሮች እየታሰበ ይገኛል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ