የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ የፍቅር ጥግ ነው – ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል

You are currently viewing የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ የፍቅር ጥግ ነው – ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል

AMN – ሚያዝያ 02/2018 ዓ.ም

የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ የፍቅር ጥግ በመሆኑ እኛም ይህንን ፍቅር እርስ በርስ በመዋደድና በመተሳሰብ ልንገልጸው ይገባል ሲሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል አሳሰቡ።

የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት እየታሰበ ነው።

በዓሉ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌልን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮቾች በተገኙበት በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ሀይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ስርዓቶች እየታሰበ ይገኛል።

ምዕመናን ዕለቱን በጾም፣ በጸሎት እና በስግደት የክርስቶስን መከራ እና ሞት እያስታወሱ በታላቅ በተማጽኖ እያሳለፉ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነ ኢየሱስ ሱራፌል የክርስቶስ ስቅለት ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ የፍቅር ጥግ በመሆኑ እኛም ይህንን ፍቅር እርስ በርስ በመዋደድና በመተሳሰብ ልንገልጸው ይገባል ብለዋል

ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ የጠላቶቹን ይቅርታ እንደለመነ፣ እኛም ዛሬ ለሀገራችን ሰላምና እርቅ ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል’ ብለዋል።

ዕለቱን “የፍቅር ቀን” አድርገው እንደሚመለከቱት የገለፁልን የእምነቱ ተከታዮች ፍቅር ትዕግሥትና ይቅርታ ከእየሱስ ክርስቶስ በመማር የእለት ተእለት ባህል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በደሳለኝ ሙሐመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review