AMN- ሚያዝያ 02/ 2018 ዓ.ም
አስተዳደሩ የበዓል ገበያን ለማረጋጋት ምርቶች በጥራት እና በብዛት እንዲቀርቡ የወሰነው ውሳኔ ውጤት እያመጣ መሆኑን በተግባር አረጋግጠናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር ተናገሩ::
አፈ- ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ በልደታ፣ በካ እና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንሰሳት የበአል ግብይት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በግብይት ሂደቱ የአቅርቦት እጥረት እንዳይኖር የከተማ አስተዳደሩ ስኬታማ ስራ መስራቱን የገለጹት አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልከድር፣ ምርቶች ላይ አላግባብ የሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ብርቱ ቁጥጥር መደረጉ እና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በመድረስ ላይ መሆናቸውን በምልከታው ወቅት መታዘባቸውን ገልጸዋል::

ይህም አስተዳደሩ የበዓል ገበያን ለማረጋጋት እና ምርቶች በጥራት እና በብዛት እንዲቀርቡ የወሰነው ውሳኔ ውጤት እያመጣ መሆኑን በተግባር አረጋግጠናል ሲሉ ተናግረዋል።
በአንዋር አህመድ