ከንቲባ አዳነች አቤቤ 27ኛውን የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር ከተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አከበሩ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ 27ኛውን የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር ከተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አከበሩ

AMN – ሚያዚያ 4/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 27ኛውን የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል ስራ በማስጀመር ከማዕከሉ ከተጠቃሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን በጋራ አከበሩ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ፣ ይህ ዛሬ ስራ ያስጀመሩት 27ኛው የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሶስተኛ ቅርንጫፍ ነው፡፡

ከንቲባዋ በመልክታቸው ፣ የምገባ ማዕከሉ ተጠቃሚ ከሆኑ ለማህበራዊ ችግር ከተጋለጡ ፣ አልባሽ አጉራሽ ለሌላቸው የሀገር ባለውለታ፣ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻች ፣ ከአረጋዊያን እና ከአካል ጉዳተኞች ወገኖቻችንን እንኳን አደረሳችሁ ብለን በዓሉን በጋራ አክብረናል ብለዋል።

በዓሉ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ያለአንዳች ልዩነት ለሰው ልጆች ሁሉ ራስን እስከ መስጠት ያሳየንን ፍቅር፣ በአብሮነት በፍቅርና በመተሳሰብ ምሳሌነቱ በመከተል ልንኖር እንደሚገባ የሚስተምር በዓል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

እኛም በ27ቱም የተስፉ ብርሃን የምገባ ማዕከል በዚሁ በትንሳኤ በዓል ብቻ ሳይሆን ሁሌም ወገኖቻችን ስንመግብ ለዜጐቻችን ክብራችንና ፍቅራችንን የምንገልጥበትና ማህበራዊ ፍትህን የምናነግስበት ተግባር ነው ሲሉ አክለዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች መዓድ የማቋደስ መርሐ-ግብር በማዕከላቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

“መስጠት አያጎድልም” በሚል መርሕ የተደረገላቸዉን ጥሪ በመቀበል የገነቡት በጎ ፈቃደኛ “የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አቶ አብይ አበራ” እና በየቀኑ ለሚመመገብ የተረከበዉን “አኳስ ኮንስትራክሽን ፒ ኤል ሲ ባለቤት አቶ ወሰንን” በተጠቃሚዉ ወገን፣ በከተማ አስተዳደሩና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዓሉ የመተባበር፣ የመደጋገፍ እና የፍቅር በዓል ይሁንልን! መልካም በዓል ሲሉም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review