AMN- ሚያዝያ 5/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ – የዓለም ትኩረት የስበት ማዕከል መሆንዋን ቀጥላለች:: አዲስ አበባ 2019 ዓ.ም 89 ኛውን የዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) ጉባኤ ለማስተናገድ ተመርጣለች፡፡
በሉዛን ስዊዘርላንድ በተካሄደው 88ኛው ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር (AIPS) ጉባኤ ላይ፣ ኢትዮጵያ በ2019 ዓ.ም የሚካሄደውን 89ኛውን ጉባኤ እንድታስተናግድ ተመርጣለች።
ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት እያስመዘገበች ባለችው ሃገራዊ የልማት እና ዓለማቀፋዊ የዲፕሎማሲ ስኬቶች በርካታ ዓለማቀፋዊ ስብባዎች እንድታካሂድ ተመራጭ እየሆነች ትገኛለች፡፡
በሀገራችን ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ጉባኤ፣ በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር እና በመንግስት የጋራ ጥረት የተገኘ መሆኑን ከሉዛን ስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ነዋይ ይመር ገልፀዋል ፡፡

የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች ጉባኤው ለሀገራችን ብሔራዊ ኩራት ከመሆኑም በላይ፣ ተጨማሪ እድል ይዞ የሚመጣ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተደማጭነት ያላቸውን የዓለም ስፖርት ጋዜጠኞች የሚሳተፉበት ጉባኤ በአዲስ አበባ ማስተናገድ ከተማችንን ብሎም ሃገራችን ለዓለም የማስተዋወቅ እድሉ ከፍተኛ ከፍተኛ መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል፡፡