AMN – የካቲት 6/2017 ዓ.ም
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብስባ ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።
“የማካካሻ ፍትሕ ለአፍሪካውያንና ዘርዓ-አፍሪካውያን” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደውበዚህ ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ዲፕሎማቶችና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል።
ምክር ቤቱ ለሁለት ቀን በሚቆየው ስብስባ በተለያዩ አህጉራዊ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በህብረቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ምክር ቤቱ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንር ስር የሚገኙ የስድስት ኮሚሽነሮች ምርጫ ተካሄዷል።
ኢትዮጵያ ትናንት የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት ሆና ተመርጣለች።
የስራ አስፈጻሚው አካል የካቲት 8 እና 9 ቀን 2017 ዓ.ም ለሚከናወነው 38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።