አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ

AMN – ኅዳር 10/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡

በህክምናው ዘርፍ በርካታ አመታትን የተሻገረው የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት የጤና ቱሪዝም ከፍተኛውን አሻራ ያኖረ መሆኑን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ተከተል ጥላሁን በስምምነቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም ሆስፒታሉ አለም የደረሰባቸውን የጤና ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም የህክምና አገልግሎት ለህዝቡ እየሰጠ የሚገኝ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አገልግሎቱን ይበልጥ ወደ ህዝብ ተደራሽ ለማድረግ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ምርጫው ማድረጉን አንስተዋል፡፡

ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ከሚዲያ ተቋሙ ጋር በቅንጅት ሲሰራ የነበረ ቢሆንም በስምምነት ደረጃ የአሁኑ የመጀመሪያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሆስፒታሉ ኤ ኤም ኤን ባሉት የተለያዩ የሚዲያ አውታሮች የህክምና ዘርፉ ላይ ይበልጥ ለመስራት መዘጋጀቱንም የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻሚ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገበያ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ መሀመድናስር እስማኤል፣ ሚዲያው ከተማዋ የሚመጥናትን መረጃ ተደራሽ ለማድረግ በማህበራዊ ፤ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ እና በዚህም ስኬቶችን እያስመዘገበ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተለይም የከተማው ነዋሪ የሚፈልጋቸውን አገልግሎቶች መረጃ ላይ በተመሰረት መንገድ እንዲያገኝ ለማስቻል ከተለያዩ ተቋማት ጋር ስምምነቶችን በማድረግ እየሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክም ከሆስፒታሉ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በሬዲዮ፤ በቴሌቪሽን፤ በዲጂታል ሚዲያው እንዲሁም በህትመት የማሰራጫ መንገዶቹ የሆስፒታሉን አገልግሎቶች ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል፡፡

በሩዝሊን መሃመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review