አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር ጋር ተወያዩ

AMN- ኅዳር 11/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር መሀመድ ሳሊም አል ራሺዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በተለያዩ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ማሳደግ ላይ ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

ሁለቱ ወገኖች የመጀመርያውን የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ውጤት በመተግበር ረገድ የተደረሰውን መሻሻል የገመገሙ ሲሆን በቀጣይ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚካሄደዉን የሁለትዮሽ ስብሰባ ዝግጅት በተመለከተ ተወያይተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review