የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላም የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ ገለጸ

AMN – ኅዳር 16/2017 ዓ.ም

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ ለቀጣናው ብሎም ለዓለም ሰላም የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ የድርጅቱ ረዳት ዋና ጸሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የአፍሪካ አህጉራዊ የሰላም ኮንፈረንስ “የበለፀገች እና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሐፊ እና በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር)፣ ኮንፈረንሱ በውቧ አዲስ አበባ መዘጋጀቱ የተለየ የደስታ ስሜት ፈጥሮብኛል ብለዋል።

የሰላም ኮንፈረንሱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ አገራት እና ለአህጉሪቱ ወሳኝ እንደሆነም ተናግረዋል።

የዓለምን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ የአፍሪካን ሰላም መጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህ ደግሞ በጋራ ተባብሮ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሰላም የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የጋራ ጥረት እና ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ፣ ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ሰላም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review