የቬይትናም ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር ፋም ሚን ቺን በይፋዊ ጉብኝታችን ወቅት ላደረጉልን የደመቀ አቀባበል እና የክብር መስተንግዶ አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያና ቬይትናም የሚያመሳስሏቸው ብዙ የጋራ ጉዳዮች አሏቸው። ሁለታችንም ትልቅ እና ለሥራ የተነሳሳ ወጣት ሕዝብ ያለን፣ ለልማት እና እድገት የቆረጠ‍ን እንዲሁም በታሪካችን ሂደትም በፅናታችን የምንታወቅ ሀገራት ነን።