በሴቶች አደባባይ ዙሪያ 105 ሱቆችን የገነባን ሲሆን ከነዚህ ሱቆች 90%ቱን ያገኙት ከመፍረሱ በፊት እዛዉ ንግድ የነበራቸዉ ናቸው። በተጨማሪም በአካባቢው ላይ ከተለያዩ አስቸጋሪ ህይወት ውስጥ አውጥተን፣ አሰልጥነን ለስራ ያበቃናቸው ከየነገዋ የተሃድሶና ክህሎት ማበልፅጊያ ማዕከል የተመረቁ ሴቶች የሚሰሩባቸው ፀጉር ቤት፣ ካፍቴሪያ፣ ሬስቶራንት፣ የልብስ ስፌት፣ ስጋ ቤት እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ስራዎቻችንን በመንከባከብ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ የተደረጉናቸው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ