ህገ-ወጥ ስደትን መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

You are currently viewing ህገ-ወጥ ስደትን መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

AMN – መጋቢት 8/2017 ዓ.ም

በጂቡቲ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ፣ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰኢድ ኖህ ሀሰን ጋር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ህገ-ወጥ ስደት መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ኤምባሲው ከጅቡቲ ጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል እና በህገ-ወጥ የደላሎች ሰንሰለት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

ሚኒስትሩ፣ ከኤምባሲው ጋር በቅርበት በመስራት አስፈላጊውን የህግ ከለላ በሚደረግበት ሁኔታ ላይም መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review