AMN – የካቲት 12/2017 ዓ.ም
በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው በተገኙ 14 ሺ 129 ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊነት መመለስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡
ከንቲባዋ በምክር ቤት ተገኝተው ንግድን በተመለከተ ባቀረቡት ሪፖርት 31 ሺ 267 የንግድ ምዝገባና ዕድሳት ተከናውኗል ብለዋል፡፡ 53 ሺ 576 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት መሰጠቱንም ጠቁመዋል፡፡285 ሺ 622 የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት መሰጠቱንም አመላክተዋል፡፡
ከንግድ ቁጥጥርና ክትትል አኳያም በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙ 14 ሺ129 ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊነት መመለስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
በተጨማሪም የኮንትሮባንድ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘ መሰረታዊ ሸቀጥ እና ነዳጅ ምርት 18 ሺ 985 ሊትር ቤንዚን፣ 9 ሺ 434.5 ሊትር ናፍጣ፣ 189 ሊትርኬሮሲን፣ 964 ሺ 324 ሊትር ዘይት እና ቡና 48 ኬሻና 100 ኪሎ ግራም በመያዝ በአጠቃላይ ከሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡