በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር እንደሚሰሩ የጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር እንደሚሰሩ የጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ

AMN – ሚያዝያ 01 /2017

በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር እንደሚሰሩ የጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ፡፡

የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) የጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎችን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው ባነጋገሩበት ጊዜ፣ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ዕድል እንደፈጠረ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በውይይታቸው አጠቃላይ የግብርናውን ዘርፍ እንቅስቃሴ ያብራሩ ሲሆን በዚህም መንግስት ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኩታ-ገጠም የግብርና ልማት ስራዎችን ማስፋፋት፣ በግብርናው ዘርፍ የስራ ዕድል ፈጠራን ማስፋትና ዘርፉን በቴክኖሎጂ በመደገፍ እንዲዘምንና ሳቢ እንዲሆን በማድረግ ወጣቶችን ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ማድረግ እንዲሁም በግብርና ኢንቨስትመንት፣ በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት እና በሌሎች የግብርና ልማት ስራዎች ምርታማነትን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

የጌትስ ፋውንዴሽን የስራ ኃላፊዎችም በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በትብብር በመስራት የበኩላቸውን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ መግለጻቸዉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review