በአዲስ አቀራረብ እና ውብ ገፅታ 3ኛ እትሟን ይዛ ወጥታለች።
በዛሬ እትሟ
– እድሳት የተደረገለት የጎንደር ፋሲለደስ ኪነ ህንፃና የከተማዋ ኮሪደርን ከአዲስ አበባ አርአያ የልማት መነሻነት ጋር አስተሳስራ ተንትናለች፤
– የጥምቀት በዓልን የሚያደምቁ የተለያዩ ምግብና መጠጦች ሽያጫ ፋይዳቸው እስከምን? ስትል ፈትሻለች፤
በአንኳር ጉዳይዋ
– የጥር ወር ድምቀቱ የጥምቀት በዓል የህዝቦች አስተሳሳሪ ሀይማኖታዊ እሴት ስለመሆኑ የክርስትና ሃይማኖት አባቶችን አነጋግራ ይዛለች፤
በቅዳሜ ገበያ
– የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱን የሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያው ምን አስገኘ? ስልት ጠይቃ ሰፊ ማብራሪያ ይዛለች፤
– የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ግብይት ውጤታማነቱ እስከምን? ስትል የተለያዩ ሀገራት ልምዶችን ዳስሳለች፤
በመዝናኛ ገጿ
– የመዲናችንን የእረፍት ቀናት የኪነ ጥበብ መሰናዶዎችን ትጠቁምዎታለች፤
– የባህል አልባሳት እና ጥምቀት ምንና ምን ናቸው? ሌላው የጋዜጣዋ ጥንቅር አካል ነው፤
በተጨማሪም፦ ስፖርት፣ ወቅታዊና ሌሎች ዘገባዎችን ይዛ ወደ አርስዎ መጥታለች።
ከአዲስ ልሳን ጋር መልካም የጥምቀት በዓል ተመኘንላችሁ!!