በደሴ የሚገነባው የኮሪደር ልማት የከተማዋን እና በዙሪያዋ ያሉ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሀብቶቿን የሚያስተሳስር ነው፡-አቶ ጃንጥራር አባይ

You are currently viewing በደሴ የሚገነባው የኮሪደር ልማት የከተማዋን እና በዙሪያዋ ያሉ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሀብቶቿን የሚያስተሳስር ነው፡-አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም

በደሴ የሚገነባው የኮሪደር ልማት የከተማዋን እና በዙሪያዋ ያሉ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሀብቶቿን የሚያስተሳስር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ገለጹ፡፡

ለደሴ ከተማ የኮሪደር የልማት ስራ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር መካሄድ ጀምሯል።

መርህግብሩን ያስጀመሩት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የቀደመች የንግድ እና የፓለቲካ መናገሻ ደሴ ከተማ ስሟን የምትመጥን ትሆን ዘንድ ሁሉም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ።

የፍቅር እና አብሮ የመኖር ተምሳሌት የሆነችው ደሴ የእድሜዋን ልክ አለማደጓን የጠቀሱት አቶ አረጋ ለነዋሪዎቿ የተመቸች እና ውብ ከተማ በመፍጠር ረገድ ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የደሴ ከተማ ኮሪደር ልማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት መንገዶችን ከማስፋት በዘለለ የከተሞችን የመሰረተ ልማት ችግሮችን ከመሰረቱ የሚቀርፍ መሆኑን የተገነዘብንበት ነው ብለዋል።

በደሴ የሚገነባው የኮሪደር ልማትም የከተማዋን እና በዙሪያዋ ያሉ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ ሀብቶቿን የሚያስተሳስር መሆኑን ጠቅሰዋል።

ምክትል ከንቲባው በቅርቡ በደሴ ከተማ በመገኘት የቅድመ ዝግጅት ስራውን መገምገማቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬውም መድረክ ላይ ከተማዋን ለማስብ የሚደረገውን ጥረት ሁሉም እንዲያግዝ ጠይቀዋል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ :የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ እንዲሁም የደሴ ተወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

በአፈወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review