ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የስነምግባር ጉድለት በተገኘባቸው ከ1ሺህ 800 በላይ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

You are currently viewing ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የስነምግባር ጉድለት በተገኘባቸው ከ1ሺህ 800 በላይ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ

AMN – ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የስነምግባር ጉድለት በተገኘባቸው ከ1ሺህ 800 በላይ አመራሮች እና ሰራተኞች ላይ ልዩ ልዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በአድዋ መታሰቢያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን ከማጠናከር፤የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ከመደገፍ፤ የአገልጋይት እሳቤን ከማስረጽና የሚታዩ የስነ ምግባር ጉድለቶችን ከማረም ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

ሙስናን ከመከላከልና በተለያየ መንገድ ወደ ግለሰቦች የሄዱ የመንግስትና የህዝብ ሃብቶችን በክስ ሂደት ከማስመለስ ጋር በተያያዘም በቢሊዮን የሚቆጠር ሃብት ማስመለስ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ከአሁን ቀደም በነበረው የክስ ክርክር ሂደት መረጃ ከማጠናቀር ጋር በሚታዩ ክፍተቶች መንግስት ተገቢውን ውሳኔ ሲያገኝ አልነበረም ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የከተማ አስተዳደሩ በከሰሰበትና በተከሰሰበት መዝገብ 87 ከመቶ ያህል ውጤታማና ተገቢውን ውሳኔ ማግኘቱን አንስተዋል፡፡

ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማእከል ድረስ ስነ ምግባር ጥሰት በታየባቸው 90 አመራሮች ላይ ከሃላፊነት ማንሳትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቅጣቶች መተላለፋቸውን ያብራሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በ1ሺህ 726 ሰራተኞች ላይም ልዩ ልዩ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህ አመራርና ሰራተኞች የመንግስት አገልግሎት ሲያዛቡ እና ጉቦ ሲቀበሉ የተገኙ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የስነ ምግባር ጥሰት በስፋት ከታየባቸውና እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ፤ ትራንስፖርት ቢሮ፤ የአሸከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፤ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፤ ቄራዎች ድርጅት እና የፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ተጠቃሾች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወንድማገኝ አሰፋ

All reactions:

65Belachew Jebessa, Tsehhay Habte and 63 others

6

8

Like

Comment

Share

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review