ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊተገብር ይገባል -አቶ ጌቱ ወዬሳ

You are currently viewing ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አመራሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊተገብር ይገባል -አቶ ጌቱ ወዬሳ

AMN-የካቲት 04 /2017 ዓ.ም

ብልፅግና ፓርቲ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላሳለፋቸው ውሳኔዎች ተፈፃሚነት አመራሩ ሊሰራ እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ አሳሰቡ።

የብልፅግና ፓርቲ ባካሄደው ሁለተኛ ጉባኤ ላይ የማህበረሰቡን ሁንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በሀላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በሰጠቱት መግለጫ አሳስበዋል።

አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት፣ ፓርቲው ያሳለፋቸውን ውሳኔ እና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በተመለከተ በየደረጃው ለሚገኘው አመራር ብሎም ለአባላቱ ግንዛቤ እየተፈጠረ ይገኛል።

በተለይ ከማህበረሰቡ የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት መሰጠቱን የጠቆሙት አቶ ጌቱ ወዬሳ የሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን አገልጎሎቱን ለማሻሻል ትኩረት መሰጠቱን አፅንኦት ሰተዋል።

የሲቪል ሰርቪሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ከብልሹ አሰራሮች የተላቀቀ ጥራት ያለው ፈጣን እና ቀልጠፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል የሪፎርም ስራ እንደሚከናወንም ገልፀዋል።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የገለፁት አቶ ጌቱ ወዬሳ አመራሩ የመፈፀም እና የማስፈፀም አቅሙን በማጎልበት ለተያዘው ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞ ግንባር ቀደም ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ፓርቲው ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና የተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት የፓርቲውን ተልዕኮ በማይወጡ አመራሮች ላይ የምዘና ስርዓትን በማጠናከር የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም ገልጸዋል።

ፓርቲው የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ትኩረት በመስጠት የተጀመሩ አበታች ተግባራትን በተሻለ ፍጥነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም አረጋግጠዋል።

በተለይ አሰባሳቢ ትርክቶች የበላይነት እንዲጎናፀፉ በማስቻል አገራዊ አንድነት ይበልጥ እንዲጎለብት በማድረግ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋግጥ ለሚከናወኑ ተግባራት ራሳቸውን ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባቸው መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review