“ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው”- ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)

You are currently viewing “ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ ነው”- ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)

AMN – መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት እና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር ISO 21001/2018 ለመተግበርና የሙያ ብቃት ምዘና እና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን በቴክኖሎጂ በመታገዝ አውቶሜት ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህንኑ በተመለከተም ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የብቃት ምዘና ማረጋገጫ ማዕከላት እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ዓለምአቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ አንፃር ባለፉት ሁለት ዓመታት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ለመተግበር በተከናወኑ ተግባራት የሚታዩ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።

በዚሁ መነሻነት ለሌሎች ምሳሌ መሆን የሚችሉ ተቋማት እንደሚገኙ የተናገሩት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ሌሎች አዳዲስ ተቋማት ከቀድሞዎች ልምድ በመውሰድ ራሳቸውን የማዘመን ሥራ ውስጥ የሚገቡበትን ሁኔታ ለመፍጠር መድረኩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

የሥልጠና እና የምዘና ሥርዓቱን ለማዘመን የሙያ ብቃት ምዘናና ሰርተፊኬሽን ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የታገዘ አውቶሜት የማድረግ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ጠቁመው

የጥራት ሥራ አመራር ስርዓቱን በሚጠበቀው ደረጃ ለመተግበር ተቋማት ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑም ማሳሰባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review