ይህ ስፍራ ከዚህ ቀደም ለእይታ የማይመች፣ እጅግ ቆሽሾ የነበረ እና ማንም መለስ ብሎ አይቶት የማያውቀውን አካባቢ ወደ ሃብትነት ፣ ትልቅ መዝናኛ እና የህዝብ መዋያና መናፈሻ መቀየሩ መቻሉ በጣሙን ደስ ያሰኛል ።የአካባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ::
ህዝብን በማስተባበር የተሰራው የቡልቡላ ፓርክ በርካታ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት የመዝናኛ ስፍራ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ እና ባለሃብቶች ፓርኩን ለማስዋብ ላደረጋችሁት አስተዋፅዖ ታላቅ ምስጋና ይገባችኋል።
የቦሌ ክፍለከተማ አመራሮች ወደ ህዝብ ቀርባችሁ እና አስተባብራችሁ ይህንን ድንቅ ስራ በመስራታችሁ በራሴ እና በነዋሪዎች ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::
ሌሎችም ክፍለከተሞች ከዚህ ተሞክሮ በመውሰድ ህዝቡን በማስተባበር አካባቢያችሁ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ሰዉ ተኮር የልማት ስራ መስራት የሚቻል መሆኑን ከቡልቡላ ፓርክ ልምድ እንድትወስዱ እያልኩ፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ይህ ፓርክ የእናንተ በመሆኑ በአግባቡ እንድትገለገሉበት፣ እንድትጠብቁት እና እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ::
በፎቶግራፎ እዚህ ላይ ከምትመለከቱት በአካል የበለጠ ዉብ በመሆኑ እንድት ጐበኙት እጋብዛችኋለሁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ