
AMN – ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ አቀባበል ተደርጎለታል።
ዋንጫው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚኖረውን ቆይታም ዛሬ በዲላ ከተማ መጀመሩ ተመላክቷል።
የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ ዜና ማሞ እንደገለጹት፥ ዋንጫው በዞኑ ለአንድ ወር ቆይታ ያደርጋል ።
ዋንጫው በዞኑ በሚኖረው ቆይታ ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ በቦንድ ግዥ በመሳተፍ ግድቡን ለማጠናቀቅ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።
ዋንጫው ወደ ዞኑ ሲገባ ደማቅ አቀባበል የተደረገለት ሲሆን በስነ ስርአቱ ላይ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል እንዲሁም የዞን የስራ ሃላፊዎች አባገዳዎችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡