የገና በዓል ግብይት ሳምንቱን ሙሉ መሆኑ መልካም ነው ሲሉ ሸማቾች ገለጹ

  • Post category:ልማት

AMN-ታህሣሥ 26/2017 ዓ.ም

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የገና በዓል ግብይት ሳምንቱን ሙሉ መሆኑ መልካም ነው ሲሉ ሸማቾች ገልጸዋል ፡፡

በአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ በገና በዓል ግብይት ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ምርቶችን የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዛሬው እለት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 9 እና 11 ሸማቹን ለማገልገል ሳምንቱን ሙሉ ክፍት የሚሆኑ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እይተካሄዱ በመሆኑ የተሻለ ግብይት መኖሩ ተመልክቷል።

በሸመታ ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ኢግዚቢሽኑ መዘጋ ጀቱ እንዳስደሰታቸው እና አቅርቦት እና ቁጥጥሩ መልካም መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመደረጉ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review