ኮሩ ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ለማጥፋት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን አስታወቀ

AMN ታሕሣሥ 27/2017 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ኮር የህገወጥ ቡድኑን ሎጀስቲካዊ አቅርቦት በማቋረጥ እና ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን በማጥፋት ቀጠናውን ከአሸባሪዎች ነፃ የማድረግ ተልዕኮውን አጠናክሮ መቀጠሉን ሌተናል ኮሎኔል አለልኝ መሀሪ ገልፀዋል ።

ሌተናል ኮሎኔል አለልኝ መሀሪ በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ በርካታ ተተኳሽ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በተደረገ ትብብር ከነአዘዋዋሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ገልፀው ለዚህም እውነተኛ መረጃ ከመሥጠት ጀምሮ ማህበረሰቡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነበረው ብለዋል ።

ህገወጥ ቡድኑ አሁን ላይ በውጊያ ማሳካት ያልቻለውን ድል ወደ ከተሞች ሰርጎ በመግባት ሁከት እና ግርግር ለመፍጠር ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልፀው ሠራዊቱ ቀጠናውን በተጠንቀቅ እየጠበቀ በመሆኑ ተልዕኮውን ማክሸፍ ተችሏል ማሏል ማለታቸውን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review