የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት ተካሄደ

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት መርሐግብር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ በ2016 የትምህርት ዘመን በሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች፤ ምስጉን መምህራን ፣ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች፣ ባለተሰጥኦ ተማሪዎች እና ለትምህርት ልማትና እድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦች በተለያዩ ዘርፎች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በልዩ ተሸላሚ ዘርፍ አርቲስት አለማየው እሸቴ ተሸላሚ ሆኗል።

የሽልማት እና የእውቅና መርኃ ግብሩ ትልቁ ዓላማ ውጤታማ ተማሪዎችን እና ምስጉን መምህራን እንዲሁም የትምህርት ዘርፉ እንዲያድግ የላቀ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ግለሰቦችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት መሆኑ ተገልጿል።

የሽልማት በመርኃ ግብሩ በኢትዮጵያ በይዘትም በአይነትም የመጀመሪያ ነው ተብሏል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የተማሪዎች ሽልማት በአዋጅ የተቋቋመ በኢትዮጵያ ብቸኛው እና የመጀመሪያው ብሔራዊ የሽልማት ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review