ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍ አይ.አር.ሲ ገለፀ

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከኢንተርናሽል ሬስኪዩ ኮሚቴ (አይአርሲ) ፕሬዘዳንት ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስቴሩ ግጭት በተከሰተባቸው የሃገሪቱ አካባቢዎች የክትባት ተደራሽነትን ለማሳደግ ከአይአርሲ ጋር በትብብር መስራቱን መቀጠል እንደሚፈልግ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

አጠቃላይ የጤና ስርአቱን ማሻሻል ላይም አይአርሲ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

የአይአርሲ ፕሬዘዳንት እና ዋና ስራ አስኪያጅ ዴቪድ ሚሊባንድ፤ አይአርሲ በኢትዮጵያ በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው ማህበረሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ጤና ሚኒስቴር ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አይአርሲ እንደሚደግፍ የተናገሩት የድርጅቱ ፕሬዘዳንት፤ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋገጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢንተርናሽል ሬስኪዩ ኮሚቴ (አይአርሲ) በሰብአዊ ቀውሶች የተጎዱ ሰዎችን በመርዳት፣ እንዲያገግሙ እና ህይወታቸውን እንዲገነቡ ለመርዳት በተለያዩ ሀገራት ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት ሲሆን በግጭት እና በአደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጤናን፣ ደህንነትን፣ ትምህርትን፣ እና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ወደ ነበረበት ለመመለስም ይሰራል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review