ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ማሳደግ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ማሳደግ ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል-ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

AMN – ጥር 9/2017 ዓ.ም

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በቻይና መንግስት ምክር ቤት የልማት ምርምር ማዕከል ፕሬዝዳንት ሉ ሃኦ ከሚመራ ልዑክ ጋር በኢትዮጵያና ቻይና የንግድ ግንኙነት ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ ውይይቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ በሁለቱ ሃገራት መካከል ጠንካራ የንግድ ግንኙነት ያለ ቢሆንም ወደፊት የላቀ ትብብር ማድረግ የምንችልባቸውን መስኮች ለይተን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

በተለይ ኢትዮጵያ ወደ ቻይና የምትልካቸውን ምርቶች ማሳደግና የሁለቱን ሃገራት ኢኮኖሚ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተጨማሪ መስኮችን የዳሰሰ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በጥራት መንድር ጉብኝታቸውም ኢትዮጵያ ለጥራት ያላትን ቁርጠኝነት አሳይተናል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review