ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪን መርቀዋል።

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪን መርቀዋል።

AMN- የካቲት 29/ 2017 ዓ.ም.

ጠቅላይ ሚኒስትዐቢይ በይፋዊ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ” ከጥቂት ዓመታት በፊት በሀገር ውስጥ ድሮን ስለማምረት ማሰብ የማይታሰብ ነበር” ብለዋል፡፡

ብዙ አይነት ችሎታ ያላቸው ድሮኖችን በራሳችን ባለሙያዎች ዲዛይን አድርጎ የማምረት አቅም ትልቅ የታሪክ እጥፋት ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ቀጣይነት ባለው የምርምር ሥራ ላይ ገበያ በማስፋት ተግባር ላይ እና በሀገር ውስጥ የስማርት ሴንሰር ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ላይ መሥራት ይገባናልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስፍረዋል።

እንደዚህ እና እንደ ሆሚቾ የተተኳሽ ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ ያሉትን አቅሞቻችንን የምናሳድገው፤ ግጭትን ለማቀጣጠል አይደለም፤ ግጭትን ለማስቀረት እንጂ ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ግጭትን በሚፈልጉ ተዋንያን ፊት ግጭትን ለማስቀረት የሚችል አቅም በመፍጠር ሰላም እና መረጋጋትን ለማፅናት ነው ፍላጎታችን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review