የጣሊያን ሴሪ አ 28ኛ ሳምንት በተጠባቂ ጨዋታዎች ተገባዷል

You are currently viewing የጣሊያን ሴሪ አ 28ኛ ሳምንት በተጠባቂ ጨዋታዎች ተገባዷል

AMN-መጋቢት 1/2017 ዓ.ም

ቅዳሜ ሁለቱ የሚላን ከተማ ክለቦች 2ለ0 ከመመራት ተነስተው 3ለ2 በማሸነፍ ጣፋጭ ድል ተጎናጽፈዋል፡፡

እሁድ ያልተጠበቀ ውጤት የተመዘገበበት የቱሪኑ መርሃ ግብር ጁቬንቱስና አታላንታ ቱሪን ላይ ያደረጉት ጨዋታ በጂያንፔሮ ጋስፔሪኒው ስብስብ 4ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የሴሪ አው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ማቲኦ ራትጊዊ የውድድር ዓመቱን 22ኛ ግቡን አስቆጥሯል፡፡

ማርቴን ዲ ሩን፣ ዴቪድ ዛፓኮስታና አዴሞላ ሉክማን ቀሪዎቹን የአታላንታ ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡

ከፍተኛ የጨዋታ ብልጫ የወሰደው አታላንታ በማሸነፉ ከመሪው ኢንተር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት አጥብቧል፡፡

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ናፖሊ በሮሜሉ ሉካኩና ጂያኮሞ ራስፓዶሪ ግቦች ፊዮረንቲናን 2ለ1 አሸንፏል፡፡

ሮማ በበኩሉ በማቲያስ ሱሌ ብቸኛ ግብ ኢምፖሊን 1ለ0 ረቷል፡፡

ዛሬ ምሽት የሚደረገው የላዮና ዩዲኒዜ ጨዋታ የ28ኛ ሳምንት የመዝጊያ መርሃ ግብር ነው፡፡

ኢንተር ሚላን በ61 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡን ሲመራ፣ ናፖሊ በ60፣ አታላንታ በ58 እንዲሁም የቲያጎ ሞታው ስብስብ ጁቬንቱስ በ52 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ይዘዋል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review