AMN – መጋቢት 9/2017 ዓ.ም
የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ከዣንዲር ፌሔይራ ዶስ ሳንቶስ ጋር ስለ ግብርና ልማት ትብብር በሁለቱ ሀገራት መካከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችና በቀጣይም የሚከናወኑ ስራዎች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የአፈር ለምነት እና ጤንነት አጠባበቅ፣ የግብርና ሜካናይዜሽን እና የግብርና ወጪ ንግድ ስራዎች በዋናነት ትኩረት አድርገው የተወያዩባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ወደፊት በትብብር አብረው እንደሚሰሩም መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በረሃብ እና ድህነት ላይ ዓለም አቀፍ ትብብር ቦርድ ሻምፒዮን እንደመሆኗ እና የብሪክስ ዓባልም በመሆኗ ወደ ፊት በግብርናው ዘርፍ ይበልጥ አብረው የሚሰሩበት ምቹ ሁኔታዎችም ላይ ተወያይተዋል፡፡