ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፑቲን በዩክሬን አዲስ መንግስት መቋቋም አለበት በማለታቸው ተበሳጩ

You are currently viewing ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፑቲን በዩክሬን አዲስ መንግስት መቋቋም አለበት በማለታቸው ተበሳጩ

AMN- መጋቢት 22/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን አዲስ መንግስት መቋቋም አለበት በማለታቸው መበሳጨታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሩሲያ በዩክሬን ያለውን ደም አፋሳሽ ጦርነት በተኩስ አቁም ካልቋጨች በሞስኮ የነዳጅ ምርት ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ እንደሚጥሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

በአሜሪካ እና በሞስኮ የዲፕሎማሲ መላላት ከተፈጠረ በክሬሚሊን እና በዋይት ሀውስ መካከል ከበፊቱ የከፋ ውጥረት ሊነግስ እንደሚችል ነው የተመላከተው፡፡

በፑቲን የተበሳጩት ትራምፕ፣ “ሞስኮ ተኩስ አቁሙን ካልተስማማች ከሩሲያ በሚመጣ የነዳጅ ምርት ላይ ሁሉ ሁለተኛውን ማዕቀብ እጥላለሁ” ሲሉ ዝተዋል።

ከዚህም ባለፈ ሁሉም ወገኖች በሰላም ድርድር ሂደቱ ቁርጠኞች መሆን አለባቸው ብለዋል፡፡

የ25 በመቶው ቀረጥ በየትኛውም ቅጽበት ሊጣል እንደሚችል የዛቱት ሪፐብሊካኑ ትራምፕ፣ ሳምንት ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ዕቅድ መያዛቸውም ተመላክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የትራምፕን ቁጣ የሚያቀዘቅዝ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይህም በዩክሬን የተኩስ አቁም ድርድርን አስመልክቶ ከዋሽንግተን ጋር ሥራዎች እንደቀጠሉ ነው ማለታቸዉ ቢቢሲ ዘግቧል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review