የአለማችን ቢሊየነር ኤለን ማስክ 100 ቢሊዮን ዶላር ከሰረ

You are currently viewing የአለማችን ቢሊየነር ኤለን ማስክ 100 ቢሊዮን ዶላር ከሰረ

AMN – ሚያዝያ 3/ 2017

አሜሪካዊው የአለማችን ቢሊየነርስ፣ የ”ኤክስ” እና የ“ቴስላ” ባለቤት የሆነው ኤለን ማስክ፣ ከአንድ መቶ ቢልየን ዶላር በላይ መክሰሩ ተገለጸ።

ኤለን ማስክ በዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ቅስቀሳ ወቅት ከመሳተፍ ጀምሮ በአስተዳደሩም ውስጥ ከተካተተ ወዲህም በአጠቃላይ በቢዝነሱ እና “ቴስላ” በተባለው የመኪና ብራንድ መቀዛቀዝና ገቢውም እያሽቆለቆለ መምጣቱ እየተነገረ ነው።

ከ4 ወራት በፊት ከ4 መቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ተመዝግቦ የነበረው የኤለን ማስክ ሀብት፣ አሁን ላይ ወደ ከ3 መቶ ቢሊዮን ዶላር መውረዱ ሀብታቸው እያሽቆለቆለ ከመጣው ቢሊየነሮች መካከል ስድስተኛው ባለሃብት መሆኑን ዘኢኮኖሚስት ዘግቧል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review