ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ ከ6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል -ግብርና ሚኒስቴር

You are currently viewing ለዘንድሮው አረንጓዴ አሻራ ከ6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተዘጋጅተዋል -ግብርና ሚኒስቴር

AMN – ሚያዝያ 3/2017

ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን ከ6 ቢሊዮን በላይ ግኞች መዘጋጀታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን እንደገለጹት፣ በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ባለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የአካባቢ ስርዓተ ምህዳር መጠበቅ ከመቻሉም ባለፈ ሀገራዊ የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 ከመቶ ማደጉን ጠቅሰዋል።

ለዘንድሮው የክረምት አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብርም እስካሁን ከ6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ከ40 ከመቶ በላይ የሚሆኑት ጉድጓዶችም ተቆፍረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዝናብ የሚያገኙና በልግ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በዚህ ወር እንደሚጀምርም መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review