ደቡብ ኮሪያ እና ሶሪያ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረቱ

You are currently viewing ደቡብ ኮሪያ እና ሶሪያ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሰረቱ

AMN – ሚያዝያ 3/2017 ዓ.ም

የሁለቱ ሀገራት መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረት፣ ለአዲሱ የሶሪያው የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት አህመድ አል ሻራ የተሻለ እድል ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እርምጃ፣ ለቀድሞው የሶሪያው በሽር አል አሳድ መንግስት ወዳጅ ለነበረችው ሰሜን ኮሪያ መርዶ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ፣ በደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቾ ታይ-ዩል እና በሶርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአሳድ አል ሻይባኒ መካከል በትናንትናው ዕለት በደማስቆ መደበኛ እንዲሆን ተደርጓል።

በሥነ ስርዓቱም፣ ሶሪያ ከ13 ዓመቱ የእርስ በርስ ጦርነት እንድታገግም ደቡብ ኮሪያ በንግድ ኢንቨስትመንት እና በሰብዓዊ እርዳታ ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን ቾ ተናግረዋል።

አል ሻይባኒ ደቡብ ኮሪያ በደማስቆ ላይ የተጣሉትን ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች እንዲነሱ በማድረግ ድጋፍ ታደርጋለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው መግለፃቸውን አልጄዚራ ዘግቧል።

ሴኡል አሁን ላይ ደማስቆን ጨምሮ 191 የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላት።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review