ህብረተሰቡ በዓልን ምክንያት አድርጎ እርድ ሲከውን የእርድ ተረፈ ምርቶች በአግባቡ በማስወገድ የከተማዋን ውበት ማስቀጠል እንደሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ አሳሰቡ፡፡
ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እሸቱ ለማ፤ የከተማዋ ነዋሪዎች ቆሻሻን የማስወገድ ባህል እንዲያጎልብቱ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ቆሻሻን የማስወገድ ባህል እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶቿ ምቹ ያልነበረች አዲስ አበባ ከተማን በተከናወኑ ተግባራት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዘመናዊ ከተማ መፍጠር ተችሏል ያሉት ዳይሬክተሩ ይህችን ከተማ ንጽህናዋን ማስቀጠል የሁሉም ሃላፊነት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ህብረተሰቡ በዓልን ምክንያት አድርጎ እርድ ሲከውን የእርድ ተረፈ ምርቶችን በአግባቡ በማስወገድ የከተማዋን ውበት ማስቀጠል እንደሚገባው ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ

See insights and ads
All reactions:
5656