ሀገራችንን ማስዋብ እና የልጆቻችንን ህይወት በተስፋ እና በተድላ የተሞላ ማድረግ ቀዳሚው ፍላጎታችን ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትንሳኤ በዓልን ከካዛንችስ አካባቢ በኮሪደር ልማት ተነስተው በገላን ጉራ ከገቡ ነዋሪዎች ጋር አክብረዋል፡፡
በገላን ጉራ መንደር ነዋሪው የተሻለ መሰረተ ልማት ተሟልቶለት ኑሮውም ተሻሽሎ በመመልከተቻው መደሰታቸውን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተናገሩት፡፡
ቃል በተገባው መሰረት ካዛንችስ በአጭር ጊዜ ለምታ መለወጧን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለልጆቻችን የተሻለ ኑሮ የሚኖሩበትን መደላድል እየፈጠርን ነው ብለዋል፡፡ነዋሪዎቹ የተለወጠውን የቀድሞ ሰፈራቸውን እንዲጎበኙም ጋብዘዋል፡፡
ከተማችን ተጎሳቁላ እና ጎስቁላ እያየን ዝም ማለት አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቀይረው ያልነው መጪውን ዘመን ለማሳመር ነው በዚህም ተሳክቶልናል ብለዋል፡፡
ሀገራችንን ማስዋብ እና የልጆቻችንን ህይወት በተስፋ እና በተድላ የተሞላ ማድረግ ቀዳሚው ፍላጎታችን ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለገላን ጉራ ነዋሪዎች ማዕድም አጋርተዋል፡፡
በሰብስቤ ባዩ