በክልሉ የልማት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎችን ለመመለስ በየደረጃው ያለው አመራር የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ።
የኦሮሚያ ክልል የዘጠኝ ወራት የመንግስትና የፓርቲ የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ገልመ አባገዳ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፣ የመድረኩ ዓላማ ያለፉት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ውስጥ የተሳኩ ስራዎችና የታዩ ክፍተቶችን በአግባቡ በመፈተሽ ለቀጣይ የጋራ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው ብለዋል።
አራተኛው ሩብ ዓመት የበጀት ዓመቱን የልማት ስራዎች የምናጠናቅቅበት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ከስራ አፈፃፀም ግምግማው በተጓዳኝ የ2018 በጀት ዓመት የልማት ዕቅድ ዝግጅት ያለበትን ሁኔታ በአግባቡ በመፈተሽ ልናሳካ ያሰብነውን ግብ ያማከለ መሆኑ የሚፈትሽበት መድረክ ነው እንደሆነም መግለፃቸውም ኢዜአ ዘግቧል፡፡