በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ በርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የሊቀ ጳጳሱ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ቅዳሜ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች በሚገኙበት በቫቲካን ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደሚፈጸም ተነግሯል፡፡
በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮልዲሚር ዘለንስኪ፣ የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ፣ የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር እንዲሁም የዌልሱ ልዑል ዊሊያም እንደሚገኙ ቫቲካን አረጋግጣለች፡፡
በሥርዓተ ቀብሩ ላይ ለመገኘት ከፍተኛ ቁጥር ያለው የእምነቱ ተከታይ ወደከተማዋ በመግባት ላይ እንደሚገኝም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ምዕመኑ የአበባ ጉንጉን እና መስቀል በመያዝ በፖፕ ፍራንሲስ ህልፈት የተሰማውን ሐዘን በመግለጽ ላይ መሆኑም ተመላክቷል፡፡