በኢትዮጵያ እና በግሪክ መካከል ያለው የመንግስታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

You are currently viewing በኢትዮጵያ እና በግሪክ መካከል ያለው የመንግስታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል – አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

AMN – ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ እና በግሪክ መካከል ያለው የመንግስታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ገለጹ፡፡

በግሪክ የፓርላማ አባልና የኦርቶዶክስ ኢንተርፓርሊያመንት ጉባኤ (IAO) ኃላፊ ዶ/ር ማክስሞስ ቻራኮፖሎስ የተመራ የልኡካን ቡድን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የልኡካን ቡድኑ አባላት ከአቶ ታገሰ ጫፎ እና በምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እና የምዕራብ አውሮፓ ሀገራት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የወዳጅነት ኮሚቴ አባላት ጋር መክረዋል፡፡

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንደገለጹት፣ ሁለቱ አገራት ለበርካታ ዓመታት ያዳበሩት ጠንካራ የመንግስታት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በግሪክ ፓርላማ አባልና የኦርቶዶክስ ኢንተርፓርሊያመንት ጉባኤ (IAO) ኃላፊ ዶ/ር ማክስሞስ ቻራኮፖሎስ በበኩላቸው፣ ግሪክ የአውሮፓ ህብረት አባል እንደመሆኗ ኢትዮጵያን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ለማቀራረብ እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review