በደቡብ አፍሪካ በተነሳ ሰደድ እሳት ከ190 በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ

You are currently viewing በደቡብ አፍሪካ በተነሳ ሰደድ እሳት ከ190 በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቀሉ

AMN ሚያዚያ 20/2017 ዓ.ም

ባለፈው አርብ በደቡብ አፍሪካ በቶካይ ቴብል ተራራ አቅራቢያ የተነሳው ሰደድ እሳት አሁንም ቀጥሏል።

የኬፕታውን ከተማ የእሳት አደጋ ተከላካዮች እንደገለጹት፣ እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ቢሆንም፣ እሳቱ ወደ ቦይስ ድራይቭ፣ ካልክ ቤይ፣ ፊሽ ሆክ እና ኖርድሆክ አካባቢዎች ተዛምቷል ብለዋል።

በዚህም ተንከባካቤ የሌላቸው 48 ደከሞችን ጨምሮ 198 አባወራዎች ተፈናቅለዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል አካባቢዎች መንገዶች ተዘግተዋል፣ ሁኔታውን ለመቆጣጠርም በ12 ሰዓታት ፈረቃ የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እየሰሩ እንደሚገኙም ተመላክቷል፡፡

በአካባቢው ያለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ እሳቱን እያባባሰው ከመሆኑም ባለፈ፣ ቃጠሎው አስቸጋሪ በሆኑ ተራራማ ቦታዎች ላይ የተከሰተ በመሆኑ በምድር ላይ ተጉዘው እሳቱን ለመቆጣጠር ለሚሞክሩ ሰራተኞች አዳጋች እንደሆነባቸው ከአየ ዊትነስ እና አይ ኦ ኤል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review