የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነት ጫና ሕብረተሰቡን እንዳይፈትን ሰፊ ስራዎች እየሰራ መሆኑ ተመላከተ

You are currently viewing የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነት ጫና ሕብረተሰቡን እንዳይፈትን ሰፊ ስራዎች እየሰራ መሆኑ ተመላከተ

AMN-ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ከምክርቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው በከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነት ጫና ሕብረተሰቡን እንዳይፈትን ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከግብርና ምርቶች ጋር በተያያዘ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

የተቀመጠውን መመዘኛ የሚያሟሉ 216 የእሁድ ገበያዎች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በመግለጽ በሕብረተሰቡ የሚነሱባቸው ጥያቄዎች ላይ ክትትል በማድረግ በተሻለ መንገድ እንዲሰሩ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በተማሪዎች ምገባ ፤ የትራንስፖርት እና የቤት አቅርቦት ላይ የከተማዋ ነዋሪዎችን ጫና መቀነስ የሚችሉ ስራዎች እንደተሰሩ ምክትል ከንቲባው በማብራሪያቸው ላይ አንስተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review