ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ

You are currently viewing ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ

AMN – ሚያዝያ 23/2017

ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን በምትገኘው ኦዴሳ ከተማ ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት መፈጸሟ ተገልጿል።

ሀገሪቱ ጥቃቱን የፈጸመችው አሜሪካ እና ዩክሬን ለወራት ከዘለቀ ብርቱ ድርድር በኋላ

የተፈጥሮ ሐብት ስምምነት መፈራረማቸው በተነገረ በሰዓታት ውስጥ ነው።

በተከታታይ ተፈጽሟል በተባለው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቱ በትንሹ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ተጨማሪ አምስት ደግሞ መቁሰላቸውን የከተማዋ አስተዳዳሪ ኦሌህ ኪፐር መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አስተዳዳሪው በጥቃቱ በጋራ መኖሪያ ቤት ህንጻዎች እንዲሁም በሱፐርማርኬት እና በትምህርት ቤት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ስለ ጥቃቱ እስካሁን በሩሲያ በኩል የተባለ ነገር የለም።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review